Telegram Group & Telegram Channel
ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፬
#በነገረ #ክርስቶስ #ላይና #በምሥጢረ #ሥላሴ #ላይ #የተነሡ #ሌሎች #ከሓድያን

፩) መነናውያን:- እነዚህ በማኒ ክሕደት ጸንተው የሚኖሩ ናቸው። በትርጓሜ የሚታወቁ ሁለት ማኒዎች አሉ። አንደኛው ማኒ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ "ይህች ዓለም መጋቢ፣ አስተዳዳሪ የላትም፣ ክረምትና በጋ መዓልትና ሌሊት በልማድ ይፈራረቃሉ" ብሎ ሀልዎተ እግዚአብሔርን የካደ ሰው ነው። በእግዚአብሔር እንደልቤ የተባለ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ለእርሱ ምላሽ የሚሆን አንድ አርእስት ጽፎለታል። መዝ. ፬ የተጻፈው ለማኒ ተግሣፅ ነው። ሁለተኛው ማኒ በሐዲስ ኪዳን ዘመን የተነሣ ሲሆን ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ ሰው መስሎ በምትሐት ታየ እንጂ ሰው አልሆነም ብሎ የካደ ሰው ነው። ምትሐት ማለት መስሎ የሚታይ ግን ያልሆነ ማለት ነው። የሚዳሰስ የሚመስል ግን የማይዳሰስ ማለት ነው። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀበለ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተሰቀለ ተብሏል (ዮሐ. ፲፱፣፳፰፣ ማቴ. ፬፣፪፣ ማር. ፲፩፣፲፪)። ምትሐት ደግሞ እንደ ጥላ ስለሆነ አይራብም፣ አይጠማም፣ አይሰቀልም። ስለዚህ የመነናውያን ክሕደት በሐዲስ ኪዳን መሠረት የለሽ ነው ማለት ነው። ቅዱስ ቄርሎስም "እስመ ኢይክል ጽላሎት ሐሚመ" ብሎ ተናግሯል (ድርሳነ ቄርሎስ ፲፩)። በዳግም ትንሣኤ ቶማስ እንዲዳስሰው ያደረገውም ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነው።

፪) ሐራጥቃ:- እነዚህ ደግሞ ቃል ሥጋ ኮነ የሚለውን የወንጌላዊው ዮሐንስን ጽሑፍ ምክንያት አድርገው ቃል ተለውጦ ሥጋ ሆነ የሚሉ ናቸው። አምላክ ሰው ሲሆን አምላክነቱ ተለውጦ ሰው ሆነ የሚሉ ናቸው። ካለመኖር ወደመኖር (እምኀበ አልቦ ኀበቦ) መጥቶ የተፈጠረ ፍጥረት መለወጥ ይስማማዋል። እግዚአብሔር ግን በዘመን ብዛት የማይለወጥ አምላክ መሆኑን ሐራጥቃዎች አልተረዱም። ራሱ እግዚአብሔር "እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም" ብሎ በነቢዩ አድሮ ተናግሯልና (ሚል. ፫፣፮፣ መዝ. ፻፩፣፳፯)። ስለዚህ ትክክለኛው አስተምህሮ ሰው አምላክ ሲሆን ሰውነቱ አልተለወጠም። ከሰውነቱ ሳይለወጥ አምላክነትን ገንዘብ አደረገ እንጂ። አምላክ ሰው ሲሆንም ከአምላክነቱ አልተለወጠም። ከአምላክነቱ ሳይለወጥ ሰውነትን ገንዘቡ አደረገ እንጂ። ዘእንበለ ውላጤ (ያለመለወጥ) እያልን የምናስተምረው ትምህርት ይህንን ነው።

፫) ፎጢኖስ:- የቃል ህልውና ከማርያም ወዲህ ነው ብሎ የካደ ሰው ነው። ይኽውም ወልደ እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያልነበረ ነው። ፍጡር ከሆነች ከድንግል ማርያም የተገኘ ነው የሚል ነው። ነገር ግን ወልደ እግዚአብሔር ቅድመ ተዋሕዶ በቃልነቱ ጸንቶ የኖረና እናቱን ድንግል ማርያምን የፈጠረ አምላክ ነው። ድንግል ማርያምም ፈጣሪዋን በሥጋ የወለደች ናት። "ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ። ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው። ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ። እርሱም እናቱን በጥንተ ተፈጥሮ በሐዲስ ተፈጥሮ ፈጠረ። ነሥአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጠረ። ከእርሷ እርሱ የፈጠረውን ሥጋችንን ተዋሐደ" እንዲል (ሃይ.አበ. ፵፯፣፪)። ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም በፊት እንደነበረ ራሱም ተናግሯል። "ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለኹ አላቸው" እንዲል (ዮሐ. ፰፣፶፰)። በተጨማሪም "አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስኽ ዘንድ አክብረኝ" ብሏል (ዮሐ. ፲፯፣፭)።

፬) መርቅያን:- ቃለ እግዚአብሔር በአካላዊነት ያለ ሳይሆን ዝርው ነው ያለ ከሓዲ ነው። ይኽውም እንደ እኛ ቃል ያለ ነው። እኛ ስንናገር ድምፃችን አካል ያለው እንዳልሆነ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም አካል ያለው አይደለም ማለቱ ነው። ነገር ግን የሰውን ቃል (ድምፅ) ካስተዋልነው የሰው ነው እንጂ ሰው አይደለም። የእግዚአብሔር ቃል ግን የእግዚአብሔር ተብሎ የሚነገር ብቻ ሳይሆን ራሱም እግዚአብሔር ነው። "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" እንዲል (ዮሐ. ፩፣፩)። የፍጡራን ቃል ዝርው ሲሆን ነው። የእግዚአብሔር ቃል ግን አካላዊ ነው። "ወለዝንቱ ስም ዘውእቱ ቃል ንሌብዎ እምሠለስቱ ቃላት። ይህንን ስም ከሦስቱ ቃላት ለይተን እናውቃለን። እነዚህም አተርጋዎን፣ አአትሪኮን፣ ቦርፎሪኮን ናቸው" እንዲል (ሃይ.አበ.፲፫፣፳፪)። አተርጋዎን የሚባለው የሰው ቃል ነው። ቦርፎሪኮን የሚባለው ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ቃል ነው። ይኽውም ለእነርሱ የተሰማው ድምፅ ዝርው መሆኑን ያሳውቃል። ለእነርሱ የተሰማውን ዝርው ድምፅ (ቃል) የተናገረው ግን አካላዊ ቃል መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ይኽውም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አካላዊ ቃል ሲሆን ለሐዋርያትና ለሕዝቡ ሲያስተምር የተሰማው ቃሉ (ድምፁ) ግን ዝርው እንጂ አካል ያለው እንዳልሆነ ልብ ማድረግ ይገባል። አአትሪኮን የሚባለው የእንስሳት ድምፅ (ቃል) ነው። ድምፅ የሚባለው የሚሰማው ሲሆን ቃል የሚባለው የድምፁ መልእክት (ፍሬ ነገር) ነው።

፭) አቡሊናርዮስ:- ይህ ደግሞ ለክርስቶስ ሥጋዊ ነፍስና ልቡና የለውም። በሥጋዊ ነፍሱና ልቡ ምትክ መለኮቱ ሆነው ያለ ከሓዲ ነው። አቡሊናርዮስና ተከታዮቹ እንዲህ ያሉት ቃል ሥጋ ሆነ አለ እንጂ ቃል ነፍስን ሆነ አይልም ብለው ነው። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ሰውን ነፍስም፣ ሥጋም ብለው ይጠሩታል። ሥጋ ሲጠራ ነፍስን ዘንግተው አይደለም። "ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና" እንዲል (መዝ. ፻፴፭፣፳፭)። መቼም በዚህ ጊዜ ነፍስን ዘንግቶ አይደለም። ምክንያቱም ነፍስ የሌለው ሥጋ መጀመሪያውንም ምግብን አይበላምና ነው። ሬሳ ሲበላ አይተን አናውቅም። ነፍስ ስትጠራም ሥጋን ዘንግተው አይደለም። ለምሳሌ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ "ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውሃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም" ብሏል (፩ኛ ጴጥ. ፫፣፳)። መቼም ስምንት ነፍስ የዳነባት ሲል እነኖኅ የዳኑት ከነሥጋቸው ነውና። ይህን የመሰለ ራሱ ክርስቶስም ብዙ ቦታ ተናግሯል። ራሱን ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ እያለ ጠርቷል። በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ መሆኑንም እያሰበ ተናግሯል። ራሱን ብዙ ጊዜም የሰው ልጅ እያለ ጠርቷል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑንም እያሰበ ተናግሯል። ክርስቶስን ነፍስ የለውም ካሉ ፍጹም ሰው አይደለም ያሰኝባቸዋል። ነፍስ የሌለው ሰው የለምና። ክርስቶስ ነፍስ እንዳለው ግን "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዘነች በዚህ ቈዩ፥ ከእኔም ጋራ ትጉ አላቸው" ተብሎ ተገልጿል (ማቴ.፳፮፣፴፰)። ስለዚህ ቃል ሥጋ ኮነ ሲል በሥጋ በጠቅላላው የሰውን ማንነት መግለጥ ስለሆነ ነፍስን አልነሣም አያሰኝም። በነፍሱ ምትክ መለኮቱ ሆነው ለማለት አያስኬድም። ይህንን ትምህርት ውድቅ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በዕለተ ዓርብ መለየቱ ነው። በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መካከል ተነሣ እንላለን። ሞት ማለት የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው። በነፍሱ ምትክ መለኮቱ ነው ካሉ መለኮት ከሥጋ ተለየ ያሰኛል። መለኮት ከሥጋ ከተለየ ደግሞ መለኮት የሌለበት ቦታ አለ ያሰኛል። መለኮት ግን የማይኖርበት ቦታ የለም።

tg-me.com/orthodoxzelalemawit/6498
Create:
Last Update:

BY አንዲት እምነት ✟✟✟

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodoxzelalemawit/6498

View MORE
Open in Telegram

አንዲት እምነት Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

That growth environment will include rising inflation and interest rates. Those upward shifts naturally accompany healthy growth periods as the demand for resources, products and services rise. Importantly, the Federal Reserve has laid out the rationale for not interfering with that natural growth transition.It's not exactly a fad, but there is a widespread willingness to pay up for a growth story. Classic fundamental analysis takes a back seat. Even negative earnings are ignored. In fact, positive earnings seem to be a limiting measure, producing the question, "Is that all you've got?" The preference is a vision of untold riches when the exciting story plays out as expected.

What Is Bitcoin?

Bitcoin is a decentralized digital currency that you can buy, sell and exchange directly, without an intermediary like a bank. Bitcoin’s creator, Satoshi Nakamoto, originally described the need for “an electronic payment system based on cryptographic proof instead of trust.” Each and every Bitcoin transaction that’s ever been made exists on a public ledger accessible to everyone, making transactions hard to reverse and difficult to fake. That’s by design: Core to their decentralized nature, Bitcoins aren’t backed by the government or any issuing institution, and there’s nothing to guarantee their value besides the proof baked in the heart of the system. “The reason why it’s worth money is simply because we, as people, decided it has value—same as gold,” says Anton Mozgovoy, co-founder & CEO of digital financial service company Holyheld.

አንዲት እምነት from us

Telegram አንዲት እምነት ✟✟✟
FROM USA